የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከከተማዋ ወ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከከተማዋ ወጣቶችና ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር የጋራ የአፍጥር ፕሮግራም አካሄደ

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከከተማዋ ወጣቶችና ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር የጋራ የአፍጥር ፕሮግራም አካሄደ

የካቲት 20 ቀን 2018 ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የተቀደሰውን የረመዳን ጾም ምክንያት በማድረግ ከከተማዋ ወጣቶችና ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር የጋራ የአፍጥር መርሃ-ግብር አከናወነ።

በታላቅ ድምቀት በተከናወነው በዚህ የአፍጥር ፕሮግራም ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የቢሮው የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ታዋቂ ስፖርተኞችና የተለያዩ የወጣቶች አደረጃጀት ተወካዮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊው አቶ በላይ ደጀን፤ የረመዳን ወር የመረዳዳት፣ የመተሳሰብና የአብሮነት እሴቶች የሚጎሉበት ታላቅ ወር መሆኑን ገልጸዋል።

ቢሮው መሰል የጋራ መድረኮችን ማዘጋጀቱ በወጣቶችና በስፖርቱ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከርና በከተማዋ ያለውን የአብሮነት ባህል ለማጎልበት ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

አቶ በላይ አክለውም ስፖርትና ወጣቶች ለሀገር ሰላም፣ ለልማትና ለሁለንተናዊ እድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ ወጣቱ ትውልድ በጾሙ ወቅት የሚያሳየውን የመረዳዳትና የመደጋገፍ በጎ እሴት በሌሎችም የስራ መስኮች ላይ ሊደግመው እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት የወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቡ አባላት በበኩላቸው፤ ቢሮው እንዲህ አይነት በወንድማማችነትና በአንድነት ላይ ያተኮረ መድረክ በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መርሃ-ግብሩ በስፖርቱ ቤተሰብ መካከል ያለውን መቀራረብ ከመፍጠሩ ባለፈ፣ በሃይማኖቶች መካከል ያለውን የቆየ የመከባበር እሴት የሚያንጸባርቅ መሆኑንም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.