የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማዋን ስፖርት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በቀጣይ ወራት በትኩረት እንሰራለን። አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማዋን ስፖርት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በቀጣይ ወራት በትኩረት እንሰራለን። አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ

የካቲት 26 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የቀጣይ ወራት ዕቅድ እና የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ።

በውይይቱ ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ እንደገለጹት፤ ቢሮው በቀጣይ ወራት የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በተለይም የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በተያዘው ዕቅድ መሠረት፣ በቀጣይ ወራት ከ92 ሺህ በላይ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለዚህም ስኬት ወጣቶቹ ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት የሥነ-ልቦና ዝግጁነት እንዲኖራቸው የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ተመላክቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ወጣቶቹ በገበያው ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችሏቸው ልዩ ልዩ የሙያ ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠሩ በዕቅዱ ተካቷል።

አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ በመልዕክታቸው እንደገለጹት፣ ወጣቱ የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን የዛሬው የለውጥ ባለቤት በመሆኑ በሁለንተናዊ መልኩ ሊበቃ ይገባል ብለዋል።

"የወጣቶችን አቅም ወደ ልማት በማዞር ረገድ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው" ያሉት ኃላፊው፤ ቢሮው ወጣቶች በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ በማሳደግ የከተማዋን ብልጽግና እንዲያፋጥኑ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል የከተማዋን የስፖርት ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ሰፋ ያሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

ስፖርትን የማህበረሰቡ ባህል ለማድረግና ጤናማ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት፣ የከተማዋን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማስፋፋትና የማዘመን ስራ በትኩረት እንደሚከናወን ተጠቁሟል። ይህም ስፖርተኞች በቂ የልምምድ ቦታ እንዲያገኙና ለውድድሮች ዝግጁ እንዲሆኑ ያግዛል ተብሏል።

በመጨረሻም ተተኪ ስፖርተኞችን ከታችኛው እርከን ጀምሮ በማፍራት ረገድ የተቀናጀ ስራ እንደሚሰራ ተመላክቷል።

ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በየሰፈሩና በየክለቡ እንዲጠናከሩ በማድረግ፣ አዲስ አበባን በስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማና የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.