የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራን በትኩረት እንደሚሠራ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራን በትኩረት እንደሚሠራ አስታወቀ።
የካቲት 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማዋ በሚያደርገው የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ አዳዲስ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን በሥራ ዕድል ግንዛቤ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቋል።
ቢሮው በትልትናው እለት ከክፍል ክተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣
ከአዲስ አበባ ወጣት ክንፍ እና ከአዲስ አበባ ወጣት ማህበር አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በበጀት አመቱ ባለፉት ወራት በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ በተሰሩ ስራዎችን ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ የወጣቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ሥራዎች ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም በቤት ለቤት ምዝገባና በዕቅድ ትስስር ረገድ የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣ ወጣቶች ዘንድ የሚስተዋለውን የሥራ ማማረጥ ችግር ለመቅረፍ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያስፈልግ ኃላፊው በአጽንኦት ገልጸዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተመለከተው፣ እስካሁን ድረስ ለ428,426 ወጣቶች የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ የተከናወነ ሲሆን ይህም አበረታች ውጤት መሆኑ ተጠቁሟል።
ከዚህ በተጨማሪ ከ56 ሺህ በላይ ወጣቶች የአስተሳሰብ ለውጥ (Mindset) ስልጠና መውሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የክፍለ ከተሞች የምሩቃን ምዝገባ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ አፈጻጸምም በንጽጽር ቀርቧል።
በመጨረሻም ቢሮው ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው የሥራ አውደ ርዕይ ላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች የሥራ ልምድ መግለጫቸውን (CV) ይዘው እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
እንዲሁም ሁሉም ወጣቶች በኤሌክትሮኒክ የሥራ መረጃ ሥርዓት (ELMIS/JMS) ላይ በመመዝገብ ከሚመቻቹ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቢሮው አሳስቧል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.