"የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

"የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በድምቀት ተካሄደ

"የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በድምቀት ተካሄደ

የካቲት 29/2018 ዓ.ም ወጣትችና ስፖርት ቢሮ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 😎 በማስመለከት በአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር በድምቀት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ ታላቅ መርሃ ግብር፣ “የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ነው።

ይህ የሩጫ ውድድር ከስፖርታዊ ይዘቱ ባለፈ፣ ሴቶች በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ያላቸውን የእኩልነት ጥያቄ በድምቀት ለማንጸባረቅና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ ያስጀመሩት ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እና የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

በዕለቱ በተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን፣ ዝነኞቹ አትሌቶች መሠረት ደፋር፣ ጥሩነሽ ዲባባና እጅጋየሁ ዲባባ እንዲሁም በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ተገኝተው ለዝግጅቱ ልዩ ድምቀት ሰጥተውታል።

መነሻውን ከአትላስ አካባቢ ያደረገው ይህ ውድድር ፍጻሜውን በሴቶች አደባባይ ያደረገ ሲሆን፣ አካል ጉዳተኛ ሴቶችም የ2 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በማድረግ አቅማቸውን አሳይተዋል።

በውድድሩ ማጠቃለያ ላይ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ አሸናፊ አትሌቶችና ተሳታፊዎች ተገቢው የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ይህ መድረክ የሴቶችን የአካል ብቃትና አንድነት ከማሳየቱም በላይ፣ በከተማ ደረጃ ያለውን የስፖርት ንቅናቄ ይበልጥ ያነቃቃ መሆኑን ተመላክቷል።

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.