በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገግኝውን 35 የእግር...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገግኝውን 35 የእግር ኳስ ሜዳ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመገንባት ስራ ተጀመረ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገግኝውን 35 የእግር ኳስ ሜዳ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመገንባት ስራ ተጀመረ።

የካቲት 30 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የ35 ሜዳ የእግር ኳስ ሜዳ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ ለማዘመን የሚያስችል የግንባታ ሥራ በይፋ ተጀምሯል።

ይህ ሜዳ ዘመናዊ አርቴፊሻል ተርፍ የሚነጠፍለት ሲሆን፣ ከሜዳው በተጨማሪ የሻወር፣ የሽንት ቤት፣ የG+1 ሕንፃ፣ ሦስት በአንድ (3 in 1) ሜዳ እና የተመልካች መቀመጫዎችን አካቶ የሚሰራ ይሆናል።

የግንባታ ሥራውን የሚያከናውነው ኤም ኤም ጠቅላላ ህንፃ ሥራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሲሆን፣ ፕሮጀክቱን በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ እንደሚያስረክብ ይጠበቃል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሮጀክቱ በከተማዋ የተጀመረውን የስፖርት መሰረተ ልማት የማስፋፋት አካል መሆኑን ገልጸዋል። ሜዳው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አርቴፊሻል ተርፍ የሚነጠፍለት በመሆኑ፣ ወጣቶች ብቁ ሆነው እንዲወጡና በዘመናዊ ስፍራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

ቢሮው እንዲህ ያሉ ጥራት ያላቸው ሜዳዎች በየአካባቢው እንዲገነቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አሰግደው አረጋግጠዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ምስክር ነጋሽ በበኩላቸው፤ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ላነሱት የመጫወቻ ሜዳ ጥያቄ ተግባራዊ ምላሽ መስጠት በመቻሉ ደስታቸውን ገልጸዋል። ግንባታው የኳስ ሜዳ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ላይ የያዘ በመሆኑ ለክፍለ ከተማው ስፖርት ዕድገት አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተናግረዋል።

ሥራ አስፈፃሚው የግንባታው ሂደት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብና ጥራት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.