ለሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሎ ሜትር የጎዳና...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ለሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መነቃቂያ ፕሮግራም ተካሄደ።

ለሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መነቃቂያ ፕሮግራም ተካሄደ።

መጋቢት 04 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

መጋቢት 13 ለሚካሄደው የሳፋሪኮም 5 ኪሎ ሜትር "ቅድሚያ ለሴቶች" የጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት አካል የሆነ የማነቃቂያ ፕሮግራም በእቴጌ መነን 2ኛ ደረጃ የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል።

ዘንድሮ "ሳቅሽ ያበረታል" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 5ኪሎ ሜትር ቅድሚያ ለሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ የሴቶችን ጥንካሬና ደስታ ለውጤታማነት ያለውን ሚና አጉልቶ ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

ዛሬ በተካሄደው የማነቃቂያ መርሀ ግብር በተማሪዎች መካከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የሩጫ ውድድር የተከናወነ ሲሆን፣ በክብር እንግድነት የተገኘችው የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር ለተማሪዎቹ ትልቅ መነሳሳትን ፈጥራለች።

አትሌቷ "ሳቅሽ ያበረታል" የሚለው መሪ ቃል በራሱ ትልቅ ትርጉም እንዳለውና ሴቶች በራስ መተማመንና በደስታ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያዘወትሩ አሳስባለች።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ስፖርት ከትምህርትና ከሥነ-ምግባር ጋር ያለውን ትስስር አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ "ሴቶች ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ያላቸው አስተዋጽኦ የላቀ ነው" በማለት የሴቶችን ሚና በንግግራቸው አጉልተዋል አሳይተዋል።

ስፖርታዊ ውድድሮች በትምህርት ቤቶች መስፋፋታቸው ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ ካለባቸው ጫና ተዝናንተው ለስኬት እንዲዘጋጁ የሚያግዝ መሆኑ አቶ አሰግደው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ቢሮ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ፣ ስፖርት በተማሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ገልጸው፣ በአካልና በአእምሮ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

ይህ የማነቃቂያ መርሃ ግብር ተማሪዎች ለታላቁ የሴቶች ሩጫ እንዲዘጋጁ ብቻ ሳይሆን፣ በትምህርታቸውና በጤናቸው ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ዘንድሮ ለ23ኛ ጊዜ የሚካሄደው 5ኪሎ ሜትር ቅድሚያ ለሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ መጋቢት 13 የሚካሄድ ሲሆን ከ16ሺህ በላይ ሴቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.