የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን ውስጣዊ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደረስ።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን ውስጣዊ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደረስ።
መጋቢት 04 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ውስጥ የሚታዩ ውስጣዊ የአሰራር፣ የምርጫና የተለያዩ የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ሲያካሂድ የቆየው ተከታታይ የውይይት መድረክ በጋራ መግባባት ላይ በመድረስ አጠናቀቀ።
ቢሮው የክለቡን ችግሮች ለመፍታት ከሁሉም አካላት የተመረጡ ሽማግሌዎችን በማሳተፍ ተከታታይነት ያለው ውይይት ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ ከክለቡ የደጋፊ ተውካዮች ጋር በመወያየት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ የሚሆን ስምምነት ላይ ደርሷል።
በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች እንዲሁም በክለቡ ጉዳይ በከሳሽነትና በተከሳሽነት ሲከራከሩ የነበሩ አካላት በተገኙበት ሰፊ ምክክር ተደርጓል።
በውይይቱም በሁሉም ወገኖች ዘንድ የጋራ መግባባት የተፈጠረ ሲሆን፣ የክለቡን አጠቃላይ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል "መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ" በይፋ ተዋቅሯል።
ይህ በሁሉም አካላት ስምምነት የተመሰረተው ኮሚቴ፣ የክለቡን አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ችግሮች ለመፍታት የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን አውጥቶ ወደ ተግባር እንደሚገባ ታውቋል።
በመጨረሻም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ "የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ጉዳይ ያገባኛል" የሚሉ ወገኖች ሁሉ የተዋቀረውን ኮሚቴ በአሰራር በማገዝ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል። ክለቡ ወደ ቀደመ ገናንነቱና ክብሩ እንዲመለስ ሁሉም አካል አስፈላጊውን እርብርብ እንዲያደርግ ቢሮው አሳስቧል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.