2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ

2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ

መጋቢት 05 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

"ተልዕኮን በጀግንነት፣ ስፖርትን በውጤት" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተከፍቷል።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የፖሊስ አዛዦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ስነ-ስርዓት ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፤ የከተማ አስተዳደሩ ለልማትና ለሰላም በሰጠው ልዩ ትኩረት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

አዲስ አበባን የቱሪስት መስህብና ዓለም አቀፍ ማዕከል ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ የፖሊስ ሰራዊቱ ከልማቱ ጋር ተቀናጅቶ እያከናወነ ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ጃንጥራር አክለውም ፖሊስ ለከተማዋ ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ለተመዘገቡት ስኬቶች የጀርባ አጥንት መሆኑን ገልጸው፣ ሰራዊቱ ለከተማዋ ብልፅግና እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቃላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አስራት ደኔሮ በበኩላቸው፤ ፖሊስ የሀገርን ብሎም የከተማዋን ሁለንተናዊ ሰላም የማስከበር መደበኛ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ፖሊስ ከሰላም ጥበቃው ጎን ለጎን በስፖርቱ ዘርፍ ባከናወናቸው ተግባራት የሀገርን ስምና የሰንደቅ ዓላማን በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ ያደረጉ ታዋቂ ስፖርተኞችን ማፍራት መቻሉን ሌተናል ጀኔራል አስራት በንንግራቸው ገልጸዋል።

ይህም የፖሊስ ሰራዊት ለስፖርቱ እድገትና ለሀገር ገፅታ ግንባታ እያበረከተ ያለውን የማይተካ ሚና እንደሚያሳይ አብራርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ በበኩላቸው ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ በዲስፕሊን የታነፀ በአካልና በአእምሮ ብቃት የዳበረ የሰው ሀይል ሲኖር መሆኑን ገልፀው ስፖርት ደግሞ ለዚህ ግብ ስኬታማነት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ስፖርት ለጤናማና ለአምራች ማህበረሰብ ግንባታ ያለውን ሚና የጠቀሱት አቶ አሰግደው ውድድሩ በፖሊስ አባሉ ውስጥ ያለውን አንድነት ይበልጥ ከማሳደጉ በላይ ኤሊት ስፖርተኞችን ለማፍራት ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታድየም በዛሬው እለት የተጀመረው ይህ ውድድርና ፌስቲቫል፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ አጠቃላይ መምሪያንና የፖሊስ ኮሌጅን ጨምሮ 11ዱም የክፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያዎች የሚሳተፉበት ይሆናል።

ውድድሩ በ6 የስፖርት አይነቶች የሚካሄድ ሲሆን፣ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚቀጥል ታውቋል።

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 

Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.