ከ30ሺ በላይ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰላም ለሁሉ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከ30ሺ በላይ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም" ታላቁ ሩጫ በድምቀት ተካሄደ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶቾ እና ስፖርት ቢሮ

ከ30ሺ በላይ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም" ታላቁ ሩጫ በድምቀት ተካሄደ

ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶቾ እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ሰፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የኢፌድሪ ሰላም ሚኒስቴር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት መነሻውን እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው"ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም" ታላቁ ሩጫ በድምቀት ተካሄደ

በዝግጅቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ለኢትዮጵያ ሰላም ምሳሌ የሆነው በሕዝቡ ሰላም ወዳድነት ነው ብለው መላው አገር ወዳድ ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል

የአብሮነት የፍቅር ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ ሁሌም የሰላም ተምሳሌት ሁና ትቀጥላች ያሉት ከንቲባ አዳነች የሁሉም ነገር መሰረት የሆነውን ሰላምን ለማጽናት መረባረብ ይገባል ብለዋል

እኛ ኢትዮጵያ ከሁሉም ነገር በላይ ምርጫችን ሰላም ነው ያሉት የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱአለም ለሰላም ድምጻችን ለማሰማት በጋራ እንሮጣለን ብለዎል

ለሰው ልጆች ሁሉ አስፈላጊ የሆነውን ሰላም በአንድ ድምጽ ለመላው ዓለም እናውጃለን ያሉት ሚንስቴሩ የታሳተፈ ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል

የሃይማኖት አባቶች፣ሴቶች፣ወጣቶች ታላቁ የሰላም ሩጫ እና ሰላምን የተመለከተ መልዕክት አስተላፈዋል።

በሩጫው ላይም ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሰላም ሚንስቴሩ ብናአልፍ አንዷለም ሚኒስትሮች፣ የአዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አምባሳደሮች ታዋቂ አትሌቶች፣ ታወቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣የሁሉም ክፍለ ከተማ አመራሮች እና ከ30ሺ በላይ የሆኑ የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዎል

በአዲስ አበባ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ በባምቢስ ፣ በዑራኤል አደባባይ ወደ ቀኝ ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ መስቀል አደባባይ እንደሚጠናቀቅ ነው የተገለጸው

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+12

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

85Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 83 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.