የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ልዑክ የከተማዋን ሁለንተናዊ ገፅታ የሚያሳይ ትዕይንት በሐረር ከተማ አቀረበ
የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ልዑክ የከተማዋን ሁለንተናዊ ገፅታ የሚያሳይ ትዕይንት በሐረር ከተማ አቀረበ
መጋቢት 22 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በድምቀት እየተካሄደ የሚገኘው 23ኛው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ውድድር እና 19ኛው የባህል ፌስቲቫል ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።
በዕለቱ በተከናወኑ መርሃ ግብሮችም የተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የራሳቸውን መገለጫ የሆኑ ባህላዊ እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን ለታዳሚው በሚያምር ሁኔታ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ልዑክ የከተማዋን ወቅታዊ ለውጥና ስኬቶች ያካተተ ደማቅ ትዕይንት ለሐረሪ ከተማ ነዋሪዎችና ለክብር እንግዶች አቅርቧል።
ልዑኩ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ባቀረበው በዚህ ትዕይንት፣ አዲስ አበባ የዘመናዊ ትምህርት ቀዳሚ መሆኗን በማስታወስ በአሁኑ ወቅት በትምህርት ጥራትና በተማሪዎች ምገባ ዙሪያ የተመዘገቡ ስኬቶችን አስተዋውቋል።
ከዚህም ባለፈ የከተማዋን ውበትና ፅዳት እንዲሁም የሰላምና ፀጥታ ስራዎችን በሚመለከት የሰላም ሰራዊቱን ሚና የሚያሳዩ ትዕይንቶች ቀርበዋል።
አዲስ አበባ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች መገኛና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኗን የሚያሳዩ ልዩ ልዩ ትርኢቶችም በታዳሚው ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈዋል።
ይህ ታላቅ ብሔራዊ ፌስቲቫል የኢትዮጵያን ብዝሃነት በማሳየት ረገድ ያለውን ሚና በማጠናከር በቀጣይ ቀናትም በተለያዩ ባህላዊ ውድድሮች ቀጥሎ እንደሚውል ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.





አስተያየቶችዎን ይተዉት.