የመዲናዋ የስፖርት ቤተሰቦች ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታወቁ
የመዲናዋ የስፖርት ቤተሰቦች ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታወቁ
መጋቢት 23 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከስፖርት ቤተሰቦች ጋር በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ውይይት አድርጎል።
በውይይት ላይ እንደተገለጸው ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የስፖርት ቤተሰቡ ከምርጫ ካርድ ከማውጣት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ሂደት ድረስ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞችና የዘርፉ ባለሙያዎች በሜዳ ላይ የሚያሳዩትን ስፖርታዊ ጨዋነትና የአንድነት እሴት ወደ ምርጫው ሂደት በማምጣት ለሰላማዊ ድባብ መፈጠር ግንባር ቀደም መሆን እንዳለባቸውም ተመልክቷል።
የስፖርት ቤተሰቦች በበኩላቸው ባስተላለፈው መልዕክት፣ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በተለይም ወጣቱ ማህበረሰብ የምርጫ ካርድ እንዲያወጣ በማነቃቃትና በምርጫ ወቅት የሰላም አምባሳደር በመሆን የከተማዋንና የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ውስጥ አሻራቸውን ለማሳረፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ቢሮው ከስፖርት ቤተሰቦች ጋር ያደረገው ይህ ውይይት በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ሁሉን አቀፍ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.