የታችኛው የማህበረሰብ ክፍል ላይ ትኩረት ያደረጉ ውድድሮች ለስፖርቱ ዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገለጸ
የታችኛው የማህበረሰብ ክፍል ላይ ትኩረት ያደረጉ ውድድሮች ለስፖርቱ ዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገለጸ
ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ከተማ አስተዳደሩን የሁሉም ስፖርቶች ማዕከል ለማድረግ የታችኛው ማህበረሰብ ክፍል ላይ ትኩረት ያደረጉ ውድድሮች ማዘጋጀት ለስፖርቱ ዕድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ጠረጴዛ ቴኒስ ለወዳጅነት በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የተካሄደው የጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር በሁለት ምድብ ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን በከተማዋ ለሚገኙ የጠረጴዛ ቴኒስ ቡድኖች መነቃቃት እንደሚፈጥር ታምኖበታል፡፡
ውድድሩ ለወጣቶች ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ የሚወዳደሩ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡
ስፖርተኞቹ የተደራጁ የስፖርት ዕድሎችን እና መድረኮችን በቀላሉ እንዲያገኙ ያስቻለ መሆኑን የገለጹት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ጠብቀው አመሸ የአካባቢው ወጣቶችን በስፖርት ለማስጠቀም የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
በውድድሩ ሻምፒዮና ለሆኑ ስፖርተኞች የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን የጠረጴዛ ቴኒስ ስፖርት ለማስፋፋት እና በቀጣይ ለሚደረጉ ውድድሮች የተሻለ ድጋፍ ካገኘ ለስፖርቱ ዕድገት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.