ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ሰኔ 23 ቀን...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ይካሄዳል::

ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ይካሄዳል

ሰኔ 18 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ከተማ አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል ''ስብዕና ልማት ለትውልድ' በሚል መሪ ቃል በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ሰኔ 23 2018 ዓ/ም እንደሚካሄድ ተገለጸ

በ114 የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት  ሲካሄድ በቆየው 9ኛው የወጣቶች ፌስቲቫል  የፍፃሜ ፌስቲቫል ውድድር አስፈላጊ በሆኑ የቅድመ ዝግጀት ስራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል

ፌስቲቫሉ በዘመናዊና ባህላዊ ውዝዋዜ፣ በሳይንስና ፈጠራ፣ በስዕልና ቅርፃ ቅርፅ፣  ታጅቦ እንደሚካሄድ የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ክብር-ዓለም ደምሴ የዘንድሮ የወጣቶች ፌስቲቫል ለየት ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል 

ከክበባት የወጡ ወጣቶች በታላላቅ መድረኮች ላይ የአገራችን ስም እያስጠሩ እንደሚገኝ ያስታወሱት ክብርዓለም  የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች በልምምድ ያካበቱትን  በመመድረክ  ስራዎቻቸውን ከማቅረብ ባለፈ ዘርፉ የሚፈልገውን ሥነ ምግባር እንዲላበሱ አሳስበዋል

የማጣሪያ ውድድሩ በዳኞች ተፈትነው ያለፉ 6 ባህላዊ እና 5 ዘመናዊ ክበባት ለፍጻሜ የሚያደርጉት ውድድር ይጠበቃል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.