ወጣቶች የስራ ፈጠራ የፍፃሜ ውድድር እና አውደ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ወጣቶች የስራ ፈጠራ የፍፃሜ ውድድር እና አውደ ርዕይ ነገ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል

ወጣቶች የስራ ፈጠራ የፍፃሜ ውድድር እና አውደ ርዕይ  ነገ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል

ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም  ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሲያካሂድ የቆየውን 9ኛውን ከተማ አቀፍ የወጣቶች የስራ ፈጠራ ውድድር የፍጻሜ ውድድር እና አውደ ርዕይ   ነገ ማክሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ቢሮው የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የስራ አጥነት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ ላለፉት ስድስት ወራት ሲያከናውን የቆየው ይህ ውድድር ከወረዳ እስከ ከተማ አስተዳደር ደረጃ ተካሂዷል። በውድድሩም ከ5 ሺህ በላይ በፈጠራ ስራ ክህሎት የካበቱ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

ነገ ማክሰኞ በአድዋ ድል መታሰቢያ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በታላቅ ድምቀት በሚከናወነው የፍጻሜ መርሃ ግብር በወጣቶች እጅ የተሰሩ ድንቅ የፈጠራ ስራዎች ለእይታ ይቀርባሉ። 

በተጨማሪም በውድድሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ወጣቶች ብቃታቸውን የሚመጥን የገንዘብና የቁሳቁስ ሽልማት በክብር እንግዶች እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።

ይህ ፕሮግራም የወጣቶችን ስብዕና ከመገንባትና የአስተሳሰብ አድማሳቸውን ከማስፋት ባለፈ  ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ለስኬት በማብቃት ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ይጠበቃል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.