9ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች የኪነ ጥበብና ፈጠራ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

9ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች የኪነ ጥበብና ፈጠራ ስራዎች ፌስቲቫል በድምቀት ተጠናቀቀ

9ኛው ከተማ አቀፍ የወጣቶች የኪነ ጥበብና ፈጠራ ስራዎች ፌስቲቫል በድምቀት ተጠናቀቀ

ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

"ስብዕና ልማት ለትውልድ" በሚል መሪ ቃል ከወረዳ ጀምሮ በክፍለ ከተማ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው የከተማ አቀፍ የወጣቶች የኪነ ጥበብ፣ የፈጠራ ስራዎችና ፌስቲቫል ዛሬ በከተማ ደረጃ በተከናወነው የፍጻሜ መድረክ አሸናፊዎችን በመለየት በድምቀት ተጠናቀቀ።

በፌስቲቫሉ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የባህል ውዝዋዜ እና የዘመናዊ ዳንስ ውድድሮች በከፍተኛ የኪነ ጥበብ ክህሎትና ወኔ የተከናወኑ ሲሆን
በባህላዊ ውዝዋዜ እናት የባህል ውዝዋዜ ቡድን አንደኛ ደረጃን ሲይዝ ሶባ እና ኖቮና አፍሮ የባህል ውዝዋዜ ቡድኖች በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በዘመናዊ ዳንስ  ተስፉ የዘመናዊ ዳንስ ቡድን አሸናፊ በመሆን ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሲሆን  ሀሌታ እና ሜዝ  የዘመናዊ ዳንስ ቡድኖች ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የፌስቲቫሉን ፍጻሜ አስመልክቶ በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አስግደው ሃይለጊዮርጊስን ጨምሮ ሌሎች የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.