"የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ለበለፀገች ኢ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

"የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" የክረምት የስፖርት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተጀመረ

"የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" የክረምት የስፖርት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ "የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የክረምት የስፖርት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በደመቀ ሁኔታ ተጀምሯል።

የዘንድሮው መርሃ ግብር መነሻውን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተመረቀው "ቀጨኔ መቀጠያ" (የእንጦጦ-ቀጨኔ መድኃኒዓለም ወንዝ ዳርቻ ልማት) መዳረሻውን ጨፌ ሜዳ በማድረግ ከ25 ሺህ በላይ ታዳጊዎችና የስፖርት ቤተሰቦች በተሳተፉበት የእግር ጉዞና የሳይክል ጨምሮ ሌሎች የስፖርት አይነቶችን በማካተት ተከናውኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ለስፖርት ዘርፉ የሰጠውን ልዩ ትኩረት አንስተዋል።

በኮሪደር ልማት እና በወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች የተገነቡት ሁሉን አቀፍ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ታዳጊዎች፣ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች እረፍት ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና በአልባሌ ቦታዎች ከማሳለፍ እንዲቆጠቡ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

ይህም ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት እንዲሁም ጤናማ፣ ደስተኛና አምራች ዜጋን ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት አቶ ዳዊት፣ ወላጆች ልጆቻቸውን በአቅራቢያቸው በሚገኙ የስልጠና ጣቢያዎች በመውሰድ ባላቸው ተሰጥኦ እንዲሰለጥኑ ጥሪ አቅርበዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.