የአዲስ አበባ ኪክ ቦክሲንግ አሶሴሽን የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በራስ ኃይሉ ስፖርት ጀመረትምህርትና ስልጠና ማዕከል ማካሄድ
ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የኪክ ቦክሲንግ የውድድር መደረኮች ሰፊ ዕድል እንዳለቸው ተገለጸ
ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
በአዲስ አበባ ያለውን የኪክ ቦክሲንግ ስፖርት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና አዳዲስ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የውድድር መድረኮቸ ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ኪክ ቦክሲንግ አሶሴሽን የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ማካሄድ ጀምሯል
ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆየው ውድድር ላይ 9 ክለቦች እንደሚሳተፉ የገለጹት የአሶሴሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ፍቀሩ ሞላ በሻምፒዮው ክለቦችን ጨምሮ በርካታ ስፖርተኞችና የስፖርቱ አፍቃሪያን እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡
ውድድሩ በታዳጊ ወጣቶች መካሄዱ ለውድድሩ የተለየ ድምቀት እንደሚሰጥ ያወሱት ፍቅሩ ተተኪ ስፖርተኞች ብቃታቸውን እንዲያሳዩና ሰፊ የውድድር ልምድ እንዲያገኙ ትልቅ ዕድል የፈጠረ መድረክ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ወጣቶች በአገር አቀፍ ውድድር ከተማ አስተዳደሩን እንዲያስጠሩ እንዲህ አይነት የውድድር መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን ያመላከቱት ፍቅሩ ክለቦች ጤናማ ፉክክር በማድረግ የቴክኒክና ታክቲክ አቅማቸውን እንዲያሳድጉበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.