ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ የሰራተኞች እና የስራ ኃላፊች ውድድር ተጠናቀቀ
ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ የሰራተኞች እና የስራ ኃላፊች ውድድር ተጠናቀቀ
ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሦስተኛው የንግድ ባክን የውስጥ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ስቴድየም ፍጻሜው ሲያገኝ ዋናው መስሪያ ቤት እና መገናኛ ዲስትሪክት የዋንጫ ባለቤት ሆኑ
ባንኩ በኢትጵያ ስፖርት የራሱን አሻራ እያሳረፈ እንደሚገኝ ያወሱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዘዳት ኢየሩሰሳሌም አምሃ የሰራተኞችን የአካል ብቃትን ለመጠበቅ እና የእርስ በእርስ ትስስርን ለማጠናከር የሚካሄዱ ውድድሮች አገር አቀፍ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው ስፓርታዊ ውድድር በሰራተኞች መካከል ያለውን ፍቅር ከማጠናከሩ በላይ ጠንካራ የአካል ብቃት ያለው ሰራተኛ ለመፍጠር እንደሚያስችል የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ፕሬዘዳንት ኮማንደር አህመድ መሐመድ ባንኩ በሃገርና ከተማዋ ልማት ላይ እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል
ጠንካራ ፉክክር በታየበት የሠራተኞች ውድድር ለዋጫ የደረሱት ዋናው መስሪ ቤት ከ መገናኛ ዲስትሪክት ባካሄዱት ፉክክር ዋና መስሪ ቤት 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሲሆን መገናኛ ዲስትሪክት የብር ሜዳልያ ኮሜርሻል ኖሚኒስ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል።
ማራኪ በነበረው በሥራ መሪዎች መካከል በተካሄደው ውድድር መገናኛ ዲስትሪከት ከዋና መስሪያ ቤት በተካሄደ ጠንካራ ፉክክር የመገናኛው የሥራ መሪዎች ቡድን 3ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮና ሲሆን ዋናው መስሪያ ቤት እና ቃሊቲ ዲስትሪክት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማኔጅመንት አባላት የውስጥ እግር ኳስ ውድድር ቂርቆስና መርካቶ ዲስትሪክት የወርቅ ሜዳልያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ፣ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ቦሌና መገናኛ ዲስትሪክት 3ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ስቴድየም በተካሄደ የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ የቢሮ ተወካይ አቶ አያሌው ታደለን ጨምሮ አንጋፋ ስፖርት ባለሙዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የባንኩ የማኔጅመንት አባላትና የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የባንኩ ሠራተኞች እና የስፖርት አፍቃሪን ተገኝተዋል።
በውድድሩ ላይ ሻምፒዮና ለሆኑ አሸናፋች የማበረታቻ የገንዘብ እና የሜዳልያ ሽልማት መበርከቱ ተመልክቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.