የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
ሐምሌ 27 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ ሠራተኞች እና የከተማዋ ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች በጋራ በመሆን አረንጓዴ አሻራቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
ቢሮው በ8ኛው ሀገር አቀፍ በአንድ ጀንበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በንቃትና በስፋት እየተሳተፈ ይገኛል።
በመርርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የቢሮው አመራሮችና ተሳታፊዎች ሀገራችንን በዕውቀት፣ በስራ እንዲሁም በለምለም አረንጓዴ ልማት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ ንጹህ አየር እና ምቹ ከባቢ አየርን ለማውረስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የከተማዋ ወጣቶችና የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለሀገር ግንባታ ከሚደረጉ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ጎን ለጎን የኢትዮጵያን ታሪክ የሚመጥን አረንጓዴ ትሩፋት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት የችግኝ ተከላ ዘመቻ ግንባር ቀደም ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.