በETFC (የአድዋ ፋይት ናይት) እና በEFN ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ስፖርተኞች እና የስፖርት ቤተሰቦች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ
የተፈጥሮ ጥበቃን ከስፖርታዊ ወንድማማችነት ጋር ያጣመሩት የድብልቅ ማረሻል አርት አትሌቶች፣ በዛሬው ዕለት ባካሄዱት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር "አዲስ አበባ የንጹሕ አየር መተንፈሻ እና የአፍሪካ ሳንባ እንድትሆን ተግተን እንሰራለን" ሲሉ ጥሪያቸውን አቀረቡ።
ከተማዋ በተፈጥሮ ያጌጠች እንድትሆን እና ንጹሕ አየርን ለመፍጠር ያለመ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር 1.5 ሚሊዮን ችግኝ መትከሏን ያስታወሱት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ስፖርት ከአካላዊ ብቃት ግንባታ ባሻገር ለተፈጥሮ ጥበቃ፣ ለሀገራዊ አንድነት እና ለጽዱ አካባቢ ግንባታ የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና ያሳየ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
በውድድር መስክ የስፖርቱ መድረክ የሚፈልጋቸው ልዩነቶች መኖራቸው ሃቅ መሆኑን ያወሳሰው የስዊት ቦክሰ ሥራ አስኪያጅ ጌታቸው መለሰ በሀገር ልማት እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ ስፖርተኞችም ሆኑ መላው ህብረተሰብ በአንድነት መቆም እንዳለባቸው ገልጽዋል፡፡
አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ መጠን፣ ለነዋሪዎቿም ሆነ ለእንግዶቿ የንጹሕ አየር መተንፈሻ እና እውነተኛ የአፍሪካ ሳንባ እንድትሆን የችግኝ ተከላ እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በጥራት ሊከናወኑ እንደሚገባ ሴዶ ማርሻል አርት ገልጽዋል
"ችግኝ መተከል ብቻውን በቂ አይደለም፤ እውነተኛው ውጤት የሚመጣው በተከሉት ችግኝ ላይ ተከታታይ እንክብካቤ ማድረግ ሲቻል ነው ያለው ጆኒ እኛ ስፖርተኞች ዛሬ የተከልናቸውን ችግኞች በባለቤትነት ስሜት ልንከባከባቸው ይገባል ብሎ ለተከለው ችግኝ ጃዝሚን የሚል ስያሜ ሰጥቷል
እንደ አረንጓዴ አሻራ ያሉ የልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች እና መሰል አገራዊ ጉዳዮች ላይ መሳፍ የሁሉም ዜጋ የጋራ ጉዳይ በመሆናቸው፣ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው በአንድነት መሰለፍ እንደሚገባ ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.