ኤሌክትሮኒክ መንግሥታዊ የግዢ አሰራር (e-GP) ከሙስና እና ከአድልዎ የጸዳ ግልጽ አሰራር እንደሚፈጥር ተገለጸ
ኤሌክትሮኒክ መንግሥታዊ የግዢ አሰራር (e-GP) ከሙስና እና ከአድልዎ የጸዳ ግልጽ አሰራር እንደሚፈጥር ተገለጸ
ኤሌክትሮኒክ መንግሥታዊ የግዢ አሰራር የe-GP ሥርዓት የግዢ አሰራር ዘመናዊ ከማድረጉም በላይ፣ በግዢ ሂደት ላይ የሚባክን ጊዜንና ሀብትን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ተገለጸ
ግዢን ፍትሐዊ፣ ግልጽ፣ ቀልጣፋና ከሙስና የጸዳ ለማድረግ ያለመው የኤሌክትሮኒክ የሕመንግሰት የግዢ ሥርዓት (e-GP) ዋና ዋና አሰራሮች እና ዲጂታል ሞጁሎች ላይ ለቢሮ ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጓል
ከግዢ እቅድ ዝግጅት እስከ ውል አስተዳደር ያሉትን አጠቃላይ የመንግስት ግዢ ሂደቶች በዲጂታል መንገድ የማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለጹት የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ሚሊዮን ኮራ የጨረታ መክፈቻ እና ግምገማ ሂደቶች በዲጂታል መንገድ በግልጽ መከናወኑ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች እኩል ዕድል ከመስጠቱ ባሻገር በወረቀት ይከናወኑ የነበሩ አሰልቺ ሂደቶችን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀርፍ ገልጸዋል
የቢሮ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የግዢ ፍላጎታቸውንና እቅዳቸውን አዘገጃጀት፣ የጨረታ ሰነዶችን አደረጃጀት፣ የኤሌክትሮኒክ ጨረታ ውድድር፣የአሸናፊዎች ማስታወቂያ፣ የቅሬታ ሰሚ ሂደቶች እና የውል ስምምነት አፈጻጸም ላይ ሰፊ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
በ2019 ተግባራዊ የሚደረገው የe-GP (Electronic Government Procurement) ግልጽነትና ፍትሐዊ ውድድር በመዘርጋት፣የጊዜና የሀብት ብክነትን በመቀነስ፣ከየትኛውም ቦታ ሆነው የመሳተፍ እድልን በማስፋት ፣አስተማማኝ ፣ቀልጣፋ ግምገማና የውል አስተዳደር የመረጃ ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.