በዘውዲቱ ሆስፒታል «በጎነት በሆስፒታል» የወጣቶ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በዘውዲቱ ሆስፒታል «በጎነት በሆስፒታል» የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስራ ስምሪት ተሰጠ

 

በዘውዲቱ ሆስፒታል «በጎነት በሆስፒታል» የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የስራ ስምሪት ተሰጠ

ነሐሴ 19 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በክረምት ወራት አጠቃላይ 14 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀ ግብሮችን በመቅረጽ የከተማውን ወጣቶች በማስተባበር በርካታ ማህበራዊና ሰብዓዊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ማዕቀፍ ውስጥ ከሚከናወኑት ታላላቅ መርሀ ግብሮች መካከል አንዱ የሆነው «በጎነት በሆስፒታል» አገልገሎት በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የጤና ተቋማት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በትላትናው ዕለትም በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ለተሰማሩ ወጣቶች ይፋዊ የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።

ለአንድ ወር ሙሉ በሚቆየውና በወጣቶች ተሳትፎ የሚከናወነው ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሆስፒታሉ የሚገኙ ታካሚዎችን በመንከባከብ፣ የጽዳትና ንጽህና ግንዛቤ ስራዎችን በማከናወን እንዲሁም የህብረተሰቡን ሰብዓዊ ፍላጎቶች በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

ቢሮው በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር ወጣቶች እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ለህብረተሰቡ እንዲለግሱ በማድረግ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ስራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.