መሰከረም 9 ለሚካሄደው የኢትዮ ፋይት ናይት (E...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

መሰከረም 9 ለሚካሄደው የኢትዮ ፋይት ናይት (EFN) ውድድር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

መሰከረም 9 ለሚካሄደው የኢትዮ ፋይት ናይት (EFN) ውድድር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ሴንተር ለሚካሄደው የኢትዮ ፋይት ናይት (EFN) ውድድር ሙሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የውድድሩ አዘጋጆች አሳወቁ።

ውድድሩን ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት አካላት ዛሬ ከሚመለከታቸው አካላትና ከፀጥታ አካላት ጋር ባደረጉት የምክክር ውይይት ለውድድሩ አስፈላጊው በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

መስከረም 9 ቀን ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በሚካሄደው በዚህ ደማቅ የስፖርት ውድድር ሚክስድ ማርሻል አርት (MMA)፣ ሞይታይ እና የቦክስ ፍልሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን ውድድሩ በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት ለተመልካቾች የሚደርስ ይሆናል።

በምሽቱ ከሚጠበቁት ታላላቅ ፍልሚያዎች መካከል የቢኒያም ሽብሬ እና የሀገረሰላም የMMA ግጥሚያ የሚጠቀስ ሲሆን በተጨማሪም ከውጭ ሀገር የመጡ ኢንተርናሽናል ተወዳዳሪዎችም የሚሳተፉበት ይሆናል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የMMA ውድድሮች ከፍተኛ ተወዳጅነትን እያተረፉ እና የውጭ ሀገር ተወዳዳሪዎችንም እየሳቡ መምጣታቸው ተመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.