ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመገንባት የተጀመረው የተማ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመገንባት የተጀመረው የተማሪዎች የማለዳ ስፖርት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጤናማና ንቁ ትውልድ ለመገንባት የተጀመረው የተማሪዎች የማለዳ ስፖርት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጠናክሮ ቀጥሏል

መሰከረም 25 ቀን 2019ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ በጠንካራ አካልና አእምሮ የታነጸ ትውልድ ለመገንባት ያለመ የተማሪዎች የማለዳ አካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር በተለያዩ የከተማዋ ትምህርት ቤቶች በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች በሳምንት ሁለት ቀን የሚያካሂዱት ይህ የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሮ በስፋት እየተገበረ ይገኛል።

በዚሁ መርሃ ግብር መሰረት በቦሌ ክፍለ ከተማ ህዳሴ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሐምሌ 19/67 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መምህራንና የትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ደማቅ የማለዳ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

የተማሪዎችን ሁለንተናዊ ጤንነትና ዝግጁነት ለማሳደግ ታስቦ የተዘረጋው ይህ መርሃ ግብር በሁሉም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ትምህርት ቤቶች በይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

ለበለጠ መረጃ

https://linktr.ee/YouthandSport1

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.