የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 38 ታዳጊ ስፖርተኞችን ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ አስመረጠ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 38 ታዳጊ ስፖርተኞችን ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ አስመረጠ
መስከረም 25 ቀን 2019ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት ልዩ ክህሎትና ተስፎ ያላቸውን ታዳጊዎች በመልመልና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት ብቁ ስፖርተኞችን የማፍራት ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል።
አካዳሚው ከነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ምልመላ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቮልቦል፣ በቦክስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ እና በጠረፄዛ ቴኒስ የስፖርት አይነቶች 38 ታዳጊዎች ማስመረጥ ችሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ለታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና የሰጠውን ልዩ ትኩረት ተከትሎ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የስልጠና ጣቢያዎችን በመክፈት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። ይህም ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ፣ ለተለያዩ ክለቦች እና ለብሔራዊ ቡድኖች በርካታ ታዳጊ ስፖርተኞችን በስፋት ለማበርከት አስችሎታል።
በመሆኑም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተመለመላችሁና ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘራችሁ ታዳጊዎች፣ አካዳሚው ባወጣው የምዝገባ ቀን መሠረት በተመደባችሁበት ካምፓስ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ያሳስባል።
https://linktr.ee/YouthandSport1
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.