የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላትን የአገልግ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላትን የአገልግሎት ጥራትና የክፍያ ተመን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ ጥናት ላይ ውይይት ተደረገ

 

የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላትን የአገልግሎት ጥራትና የክፍያ ተመን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ ጥናት ላይ ውይይት ተደረገ

መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በመዲናዋ በሚገኙ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት የሚሰጠውን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል እና ህብረተሰቡን ያማከለ የክፍያ ተመን ለመተግበር ባዘጋጀው የጥናት ረቂቅ ሰነድ ላይ የቢሮው ስትራቴጂክ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ እንደተገለጸው መዲናችን አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት እያካሄደችው ካለው ሁለንተናዊ እድገትና ከደረሰችበት ዘመናዊ ደረጃ ጋር የሚመጥን የስፖርት መሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው ተብሏል።

በከተማዋ በስፖርቱ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ዘመናዊና ሰፋፊ የልማት ስራዎች ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት የማዕከላቱ የአገልግሎት ጥራት ደረጃውን የጠበቀ እና ህብረተሰቡን ያማከለ ሲሆን በመሆኑ ጥናቱ የዚሁ ጥረት አካል እንደሆነ ተመላክቷል።

ጥናቱ በዋናነት የማዕከላቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሻሻልን፣ ዘመናዊ አሰራርን መዘርጋትን እና ህብረተሰቡን ያገናዘበ ፍትሃዊ የክፍያ ተመን መተግበርን አለማድረገ ተገልጿል።

ይህ የጥናት ረቂቅ ሰነድ በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎበትና ተጨማሪ ግብአቶች ተካተውበት ከተሻሻለ በኋላ ከህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ በሚገኙ ሁሉም አምስት (5) የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተጠቅሷል።

ለበለጠ መረጃ

https://linktr.ee/YouthandSport1


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.