የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት...

image description
- ውስጥ የቢሮ    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ከሰራተኞቹ ጋር ገመገመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ገምግሞ በቀጣይ 90 ቀናት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከሰራተኞቹ ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂደዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ስፖርቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን የማልማትና የወጣቶችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
አክለውም የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ስፖርት ሰፊ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረውና ወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ በበኩላቸው የማዘውተሪያ ስፍራዎችን አሰራር ማሻሻልና የታዳጊዎች ምዝገባ ላይ የተተገበሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂያዊና ዘመናዊ አሰራሮች ለስፖርቱ እድገት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።
አያይዘውም በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የተያዘውን መሪ ቃል ወደ ተግባር በመቀየር ለላቀ ውጤታማነት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ክብርዓለም ደምሴ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የወጣቶች ተመራጭ መዳረሻ እንዲሆኑ የተጀመረው «የስብዕና ለትውልድ» ኢኒሼቲቭ አዎንታዊ ውጤት ማምጣቱን ጠቁመዋል።
ወጣቶች ስራ ከመምረጥ ወጥተው በስራ እድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑም በግንዛቤ ፈጠራ ላይ ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ በስፖርት እና በወጣት ዘርፍ የተከናወኑ አበይት ተግባራት የቢሮውን ውጤታማነት ያረጋገጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ 90 ቀናት ትኩረት የሚሹ እቅዶች፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከሪያ ነጥቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/YouthandSport1

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.