የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 16ኛዉ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 16ኛዉ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉነን አካሄደ

16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ
16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተካሄደ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ ለከተማዋ ሁለንተናዊ የሕዝብና የኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም ለስፖርቱ ዘርፍ መሻሻል የሚበጁ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስፖርት ከውድድርና ከመዝናኛ ባለፈ የዲፕሎማሲ፣ የሕዝቦችን እርስ በእርስ መስተጋብር፣ አንድነትና አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ከንቲባዋ አክለውም በሁሉም የአዲስ አበባ አካባቢዎች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እየተስፋፉ እንደሚገኙና ስፖርት ለመስራት ለማይችሉ ወገኖች ደግሞ በኮሪዶር ልማቱ ምቹና ሰፋፊ የእግር መንገድ አማራጮች በመሰራታቸው ለስፖርቱ ተስማሚ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል።

በቀጣይም ምክር ቤቱ የታዳጊ ወጣቶችን ስልጠና በማስፋፋት ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶችን ተደራሽ ማድረግ፣ አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ በማድረግ ስፖርቱ የኢኮኖሚ አጋዥ እንዲሆን መስራት እና ከተማዋን የስፖርት ማዕከል አድርጎ አስተዋውቆ ማስገንባት ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ አስቀምጠዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት መዲናችንን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻና የስፖርት ዲፕሎማሲ ማዕከል ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/YouthandSport1


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.