
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከንቲባ አዳነች አቤቤን የብሔራዊ ቡድኑ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሾመ። ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከንቲባ አዳነች አቤቤን የብሔራዊ ቡድኑ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሾመ።
ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለእግር ኳስ ስፓርት እድገት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ዛሬ በሸራተን ሆቴል እውቅና ሰጥቷቸዋል።
ፌድሬሽኑ ለከንቲባ አዳናች አቤቤ እውቅና የሰጠው በአዲስ አበባ ስፖርት እድገት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ለሰጡት በሳል አመራር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ መርጧቸዋል
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት አዲስ አበባ ላይ እየሰራን ያለውን የስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋት እና የእግር ኳስ ሜዳዎችንን በማየት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሰጣቸው እውቅና ምስጋና አቅርበዋል
ከንቲባዋ በመልዕክታቸው የእግር ኳስ ስፖርት ሕዝባችን በስስት የሚያየው እና ታሪካችንም ከጀማሪዎቹ ፣ ነገር ግን በውጤት ከኃላ የቀረን እና የስፖርት ቤተሰቡን እያስቆጨ የሚገኝ ቢሆንም ይህን ታሪክ ለመቀየር በጋራ በመስራት እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት እንሰራለን ብለዋል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የተዘጋጀውን የእውቅና ሽልማት ለከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
All reactions:
43አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 42 others
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.