ወጣቶች የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማጎልበ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ወጣቶች የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማጎልበት በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ ሐምሌ 02 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ሰፖርት ቢሮ

ወጣቶች የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማጎልበት በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

ሐምሌ 02 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ሰፖርት ቢሮ

ወጣቶች የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማጎልበት በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጥሪ አቀረቡ።

"የወጣቶች ሚናና ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር" በሚል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የወጣቶች የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይት ከመላ ሀገሪቱ የመጡ ከ200 በላይ ወጣቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርዓያ፤ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ወጣቶች የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማጎልበት በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ለሰላምና ለተረጋጋ የሀገረ መንግስት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመድረኩ በትውልዶች መካከል መኖር ስለሚገባው ምክክር እንዲሁም በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶችን ሚና ማሳደግ ስለሚቻልባቸው መንገዶች በኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች የውይይት መነሻ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ልየታ የምክክር ምዕራፍ በአዲስ አበባ ማካሄዱ ይታወሳል።

የማህበራትና ተቋማት ተወካዮች፣ የመንግስት ተወካዮች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፤ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች የተመረጡ ወኪሎች የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን በማደራጀት በምክክሩ ላይ አቅርበዋል።

በሌሎች ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

All reactions:

20አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 19 others


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.