በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ደማቅ አሸኛኘት ይደረግላቸዋል። አቶ በላይ ደጀን ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ደማቅ አሸኛኘት ይደረግላቸዋል። አቶ በላይ ደጀን

ሐምሌ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

ኢትዮጵያ ትወዳደር ተወዳድራ ታሸንፍ" በሚል መሪ ቃል የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ምክንያት በማደርግ ሐምሌ 13 በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው ኮንሰርት ከ500ሺ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሳተፉ ተገለጸ

ቢሮው ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በጋራ በመሆን በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ላይ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን አሸኛኘት ፕሮግራምን አስመልክቶ ከአንጋፋ አትሌቶች፣ ከስፖርት ማህበራት ስራ አስፈፃሚዎች፣ ከክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ስራ አስፈፃሚዎች፣ የስፖርት ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላት ስራ አስኪያጆች፣ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሳሬም ሆቴል ውይይት አድረጎል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የኦሎምፒክ ሞቢላይዜሽን ስራዎችን ፌድሬሽኖች፣ ሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ስፓርት ማሕበራት በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበው አትሌቶችን በደማቅ ሁኔታ መሸኘት ለደማቅ ድል እንደሚያደርሰን በመረዳት በጥሩ ስነ ልቦና የአገራችን ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ አደራ የምንሰጥባት ታላቅ መድረክ ነው ብለዋል

የኦሎምፒክ ስፓርት በህዝቦች መካከል አብሮነትና ሰላምን የሚጠናከር ነው ያሉት አቶ በላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የለመደውን ድል ለማሳየት አትሌቶችን በክብር መሸኘት ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል

የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የቴክኒክና የሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ በበኩላቸው የኦሎምፒክ ችቦ በሁሉም ክልሎች ተዟዙሮ ሐምሌ 6 በአዲስ አበበ የሚካሄድ መሆኑን አስታውሰው 17 አርቲስቶች በሚሳተፉበት ኮንሰርት የኦሎምፒክ ቡድኑ ከማነቃቃት ባለፈ ሃብት ለማሳባሰብ እንደሚያስችል ገልጸዋል

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ኮንሰርት በሕዝቡ ዘንድ ለውጤቱ ተሳትፎ አለኝ የሚል ስሜት እንደሚፈጥር ገልጸው በኮንሰርቱ የኦሎምፒክ ጀግኖች ማሳተፍ ማነቃቃትን ከመፍጠሩ ባሻገር የሚመዘገበው ውጤት መንግስት ለስፓርቱ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ብለዋል

በመድረኩ ላይ የፓሪስ ኦሎምፒክ ዋና ጸሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው፣ አቃቤ ነዋይ ዶክተር ኤደን አሸናፊ ተገኝተው በቲኬት ሽያጭ እና በተካናወኑ ተግባራት ላይ ገለጻ አድርገዋል

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የሲዲነ ኦሎምፒክ ታሪክ ለመድገም አትሌቱን በስነ ልቦና ለማዘጋጀት የተዘጋጀው ኮንሰርትን ባላቸው አቅም ሁሉ እንደሚደግፉ ገልጸው አትሌቶችን የመሸኘት መርሃ ግብር ከመንግስት ወደ ሕዝብ መውረዱ እንዶስደስታቸው ገልጸዋል

የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE

👍👍👍ኢንስታግራም

https://xn--www-kqp.instagram.com/addis_abeba_youth_and...

+13

All reactions:

110Meshu Man, አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 108 others


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.