
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 35ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እየተስራ መሆኑ ተገለጸ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 35ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እየተስራ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አዳዲስ ደም ለጋሾችን በማካተት 35ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ እየስራ መሆኑን አስታወቀ
የደም ልገሳው ደሜን ለወገኔ በሚል መሪ ቃል በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተካሄደ እንደሚገኝ የገለጹት የወጣቶች ግንዛቤና ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጤናዬ ታምሩ ወጣት አደረጃጀቶችን እና በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ሕይወት የሆነውን ደም በመስጠት ሕይወት ያድኑ የሚለውን ዓለም አቅፋዊ መርህ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተናግረዋል
ዕቅዱን ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት አዳዲስ የደም ለጋሽ በጎ ፈቃደኞችን የማሳተፍ ስራ እየተስራ መሆኑን ያወሱት አቶ ጤናዬ ደም መስጠት ህይወት ማዳን በመሆኑ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርበዋል
በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ የሆነውን ደም የመለገስ በጎ ስራ በንቅናቄ ማስጀመሪያ ወቅት ከፍተኛ አመራሮችን በማካተት መከናወኑን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ በተመረጡ አደባባዮች ከተማ አቀፍ የደም ልገሳ ንቅናቄ እንደሚደረግ ጠቁመዋል
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ጋር የደም ልገሳ ፕሮግራሙን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ የላከልን መረጃ ያስረዳል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.