በበጀት አመቱ ከ369 ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በበጀት አመቱ ከ369 ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች የሰራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲሰጥ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን 1241 ማድረስ ተችሏል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በበጀት አመቱ ከ369 ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች የሰራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲሰጥ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን 1241 ማድረስ ተችሏል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሐምሌ 10 ቀንድ 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአደስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት አመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተማ አስተዳደሩን የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም አቅርበዋል።

ከንቲባዋ በሪፖርታቸው የከተማዋን ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሥራ ዕድል እና በመንግስት የድጋፍ ማዕቀፎች ዙሪያ ከ369 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደተሰጠ ገልፀዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዋችም በሕይወት ክህሎት፣ በሥራ ፈጠራ እና በንግድ ክህሎት የአመለካከት ግንባታ ዙሪያ ያተኮሩ መሆኑን ገልፀው ወጣቶች ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ እንደተቻለ ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ከማስፋፋት አኳያ በበጀት አመቱ የተሰሩ ሰራዎችን በሪፖርታቸው ሲያቀርቡ በ2015 በጀት ዓመት ከነበረበት 1,198 በ2016 በጀት ዓመት 43 ማዘወተሪያ ስፍራዎችን በማልማት ወደ 1,241 ከፍ በማድረግ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

13 የመደመር ትውልድ የህፃናትና የወጣቶች መጫወቻ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችንም በ2016 በጀት አመት ተገንብተው ለአገለልግሎት ክፍት ማድረግ መቻሉን ከንቲባዋ በአቀረቡት ሪፖርት ተመላከቷል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.