የመዲናዋ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች አረንጓ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የመዲናዋ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች አረንጓዴ አሻራቸውን በእጦጦ ፓርክ አስቀምጠዋል። ሐምሌ 14 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና የስፖርት ቢሮ

የመዲናዋ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች አረንጓዴ አሻራቸውን በእጦጦ ፓርክ አስቀምጠዋል።

ሐምሌ 14 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና የስፖርት ቢሮ

ከ10ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በእንጦጦ ፖርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀመጠዋል።

በ6ኛው ዙር የአረንጎዴ አሻራ መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የከተማውን ወጣቶች እና የሰፖርት ቤተሰቦች በማስተባበር ዛሬ በእንጦጦ ፖርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ያካሄደ ሲሆን ከ23ሺህ በላይ ችግኞች ተተክለዋል።

የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮቸ እና ስራተኞች፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ የስፖርት ማህበራት፣ አንጋፋና ታዋቂ አትሌቶች፣ የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች፣ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች እና የትራፊክ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈውበታል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት አቶ በላይ ደጀን በ6ኛ ዙር የአረንጎዴ አሻራ መርሀ ግብር የከተማውን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በማስተባበር ዛሬ የተተከሉትን 23ሺህ ችግኞችን ጨምሮ 30ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር እንደ ሀገር 7.5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የከተማው ወጣቶች አና የስፖርት ቤተሰቦች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ያሳሰቡት አቶ በላይ ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም እንደሚያስፈልግ መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2 ሚሊየን በላይ የከተማውን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በ14 የህብረተሰብ ማህበራዊ አና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በሚፈቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+23

All reactions:

209Meshu Man, አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 207 others

33

21

Like

Comment

Share

View more comments

 

Tedi - kolfe  · 

Follow

የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.