6ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በደግ ስራ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

6ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በደግ ስራዎች ታጀቦ መከናወኑ ተገለጸ ሐምሌ 14 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

6ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በደግ ስራዎች ታጀቦ መከናወኑ ተገለጸ

ሐምሌ 14 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በእንጦጦ ፓርክ ቢሮው ያካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር በበርካታ ደጋግ ስራዎች ታጅቦ መከናወኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የአየር ንብረት መስተካከል ከፍተኛ ሚና ያለውን አረንጓዴ አሻራ ከማስቀመጥ ባለፈ የተሳታፊዎች ጫማ በመጥረግ፣ ቁርስ በማቅረብ፣ እጅ በማስታጠብ እና ላስቲኮች አከባቢውን እንዳይበክሉ ታዳጊ ወጣቶች ያከናወኑት ተግባር ምሳሌ እንደሚሆን ገልጸው ለትውልድ የሚተላለፍ ጽዱና ውብ ከተማን ለመስራት ተተኪዎች ሚናቸውን እንዲያውቁ መደረጉን አውስተዋል

ችግኝ መትከል ባህል ለማድረግና ለተተኪው ትውልድ ለማሻገር ለታዳጊዎች ችግኝ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲያውቁ መደረጉ አረንጓዴ አሻራ ከመንግሥት ቅስቀሳና ከግለሰቦች ጥረት ባለፈ ሀገራዊ ቅርፅ እንዲይዝ እንደሚያስችል ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልጸዋል

ከ10ሺህ በላይ የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች በተሳተፉበት የአረንጎዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ጫማ በማጽዳት፣እጅ በማስታጠብ፣ ላስቲኮች በማንሳት፣ ቁርስ በማቅረብ የተሳተፉ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን አድምቀውታል

ወጣቶች እና የስፓርት ቤተሰቦች በ14ቱ የክረምት በጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ቢሮው ጥሪ አቅርበዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.