
ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2017 ዓ/ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2017 ዓ/ም እቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
ሐምሌ 24 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ከቢሮው ሰራተኞች ጋር ተወያየ።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ የወጣቶችን ማሕብራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሰራው ስራ አበረታች መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ መልካም የሆኑ ስራዎቻችንን በማቀጠል ማስተካከል ያለብንን ደግሞ በማሻሻል በእቅዳችን ውስጥ ያልተካተቱ ተግባራት በማካተት ለከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
ህግና አሰራሩን በመከተል ሰውን ስናገለግል የህብረተስብ እርካታ ይፈጠራል ያሉት አቶ ጥበቡ ያሉብንን ችግሮች ለመፍታት በየስራ ዘርፋችን በመወያየት እንደየ ኃላፊነታችን መስራት ይገባናል ብለዋል።
የቢሮው ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ
አዱኛ በበኩላቸው በ2016 በጀት ዓመት ሁሉም ሰራተኛ ርብርብ በማድረጉ የተሻለ የስራ አፈፃፀም መመዝግቡን አውስተው በአዲሱ በጀት ዓመት የነበረብንን ክፍተት በማረም ጥንካሬዎቻችን ማስቀጥል ይገባል ብለዋል
ቅንጅታዊ አሰራር በከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ የገለጹት ጽ/ቤት ኃላፊዋ የ2016 አፈጻጸም ምዘና ይፋ በማድረግ በቅርቡ
ለተቋማት እና ለባለሙያዎች የእውቅና መድረክ እንደሚዘጋጅ አሳውቀዋል
የቢሮው ሪፖርት እና እቅድ ያቀረቡት አቶ ጌታቸው አበባየሁ የእቅድ በጀት ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ የከተማውን ወጣቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ማልማት፤ የመንግስታዊ እና ህዝባዊ የስፖርት ተቋማትና አደረጃጀቶች፣አመራር እና አሰራር በማስተካከል የዘርፉን የመፈፀም፣የማስፈፀም አቅም ላይ የተሰሩ ስራዎች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል
አቶ ጌታቸው አያይዘውም በበጀት ዓመቱ 9,083,720 የህብረተሰብ ክፍሎች ማሳተፍ መቻሉን፣ 237,460 ወጣቶች በስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና 66,779 ወጣቶች ከብድርና ቁጠባ እንዲጠቀሙ መደረጉን 567,214 ሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ የተሰራው ስራ ስኬታማ እንደነበር ጠቅሰው በታዳጊዎች የበጋ እና ክረምት ስልጠና ከተማ አቀፍ የውድድር መድረኮች አፈጻጸማቸው ከዕቅድ በላይ መሆናቸውን አስረድተዋል
ውይይቱ የተሳተፉ የቢሮ ሰራተኞች በሪፓርቱ እና በቀረበ እቅድ ላይ ገንቢ አስተያየት ሰጥተው ላነሷቸው ጥያቄዎች የቢሮ ኃላፊዎች ጨምሮ ዳይሬክተሮች ምላሽ ሰጥተዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
All reactions:
60Meshu Man, አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 58 others
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.