በጀት አመቱ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

በጀት አመቱ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለ234ሺህ 155 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ሲቻል 42 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ክፍት ሁነዋል። አቶ በላይ ደጀን

በጀት አመቱ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለ234ሺህ 155 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ሲቻል 42 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ክፍት ሁነዋል። አቶ በላይ ደጀን

ሐምሌ 25 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2016 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት

አካሄደ።

በውይይቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ከከተማ እስከ ብሎክ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለ234ሺህ 155 የመዲናዋ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

የከተማዋን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት ለመቅረፍ በ2016 በጀት አመት በተሰራ ስራ 42 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ተገንብተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት አንዲሰጡ ክፍት መደረጋቸውን የገለፁት አቶ በላይ በከተማ አስተዳደሩ 1242 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚገኙ የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።

የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ለማድረግ እና ህብረተሰቡ በፍትሀዊነት እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን አቶ በላይ አሳውቀዋል።

የቢሮውን የ2016 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2017 በጀት አመት እቅድ አቶ ጌታቸው አበባየሁ የቢሮው የእቅድ በጀት ግምገማ እና ክትትል ዴይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዝርዝር አቅርበዋል።

የከተማወን ወጣቶች በመዲናዋ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በጀት አመቱ ቢሮው የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ በርካታ ስራዎችን መስራቱን በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመላክቷል።

ተተኪ ስፖርተኞችን ከማፍራት አኳያ በበጀት አመቱ በ11 ዱም ክፍለ ከተማ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን 257 ኤሊት ስፖርተኞችን ማፍራት ተችሏል ።

ስፖርቱን ባህል ያደረገ ማህበረሰብ ከመፍጠር አኳያ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበት እና በሚሰራበት አከባቢ የብዙሀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች እየተዘወተሩ መምጣታቸውን በሪፖርቱ የተጠቀሰ ሲሆን ከ6ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በአካል ብቃት እንውሰቃሴዎች ፕሮግራሞች ላይ ማሳተፍ ተችሏል።

በ2016 በጀት አመት በተካሄዱ የኢትዮጵያ ሻምፒና ውድድሮች ከተማ አሰተዳደሩ በተሳተፈባቸው ውድድሮችን በአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን በሀገር አቀፍ ባህል ስፖርት ውድድር እና ፌስቲቫል የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ከ18 አመት በሆላ 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት አመት በከተማዋ ወጣቶች ሁለተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የሰፖርት መሰረተ ልማት ለማሰፋፋት ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ በቀረበው እቅድ ላይ ተመላክቷል።

የልደታ ክፍለ ከተማ እና የቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤቶች የ2016 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

በውይይቱ የተሳተፋ ባለድርሻ አካላትም ቢሮው በ2016 በጀት አመት አቅዶ ያከናወናቸውን ስራዎች አድንቀው በቀጣይ ሊስተካከሉ እና ትኩረት ተደርጎባቸው ሊሰሩ ይገባቸዋል ያሏቸውን ሀሳቦች ያቀረቡ ሲሆን በቢሮው ሀላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷባቸዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+8

All reactions:

73አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 72 others


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.