
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማከናወን ጀምሯል::
በውይይቱ መድረኩ ላይ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች የሚሳተፉበት ሲሆን በዋነኛነት በ2016 በጀት ዓመት የተሰሩ እና ልምድ የሚወሰድባቸው ስራዎች እንዲሁም የህዝቡን የኑሮ ጫና ለማቅለል የተሰሩ ስራዎች የሚገመገሙበት እና በ2017 በጀት ዓመት እቅዶች ላይ ውይይት የሚደረግ ይሆናል::
በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለህዝብ በገባነው ቃል መሰረት ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት በ2016 በበጀት ዓመት ከያዝነው አጠቃላይ እቅድ በአማካይ 91% በላይ የሚሆነውን ማሳካት ችለናል ያሉ ሲሆን ይህም የአመራር ቁርጠኝነትና አንድነት እንዲሁም አዲስ የስራ ባህል በመተግበር ያሳካነው ነው ብለዋል::
ከንቲባ አዳነች አክለውም ግምገማው በ2016 በጀት ዓመት ያገኘናቸውን ስኬቶች የምናልቅበትና የምናስፋፋበት እንዲሁም በ2017 ጉድለቶቻችንን በመሙላት እና በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለነዋሪዎቿ የተመቸች ከተማ ለመገንባት እንሰራለን ብለዋል::
የግምገማ መድረኩ እና ውይይቱ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት የሚከናወን ይሆናል::
All reactions:
26አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 25 others
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.