
ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች" በሚል ቃል 21ኛው የዓለም ወጣቶች ቀን ተከበረ። ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች" በሚል ቃል 21ኛው የዓለም ወጣቶች ቀን ተከበረ።
ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችን ስፖርት በአገር አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በዓለም ለ24ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የወጣቶች ቀን
ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች" በሚል ቃል ከሁሉም ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በድምቀት አከበረ።
ለዝግጅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ የወጣቶች ቀን የአንድ ቀን ጉዳይ ሳይሆን ሁሌም ሊሰራበት የሚገባ መሆኑን ጠቅሰው አገር የምትገነባው በወጣቶች እንደመሆኑ መጠን ወጣቱ በልማት፣ በሰላም እና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዎል
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነሐሴ 12 የዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን በማለት ከሰየመ አንስቶ ያለፉት 21 ዓምታት እየተከበረ እንደሚገኝ ያስታወሱት አቶ ጥበቡ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ስናከብር አገራችን ብሎም ዓለምን ለመለወጥ በጋራ መስራት ከወጣቶች ይጠብቃል ብለዋል።
ለውይይቱ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት
የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቱሉ ጥላሁን ወጣቶችን ከቴክኖሎጂው ጋር በማስተዋወቅ አገርን የሚለውጥ ታላላቅ ፈጠራዎችን ማበርከት እንደሚቻል አስገንዝበዋል
ሀገራት ወጣት ተኮር ፖሊሲዎችንና ፕሮግራሞችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተቀርጸው ተግባራዊ በመደረጉ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን የገለጹት ዶክተር ቱሉ የዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን መከበሩ ለአዲሱ ትውልድ የተሻለ ዓለም ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
86Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 84 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.