
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!! እንኳን ደስ አለን! እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል::
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!
እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያውያን የዛሬ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል የቻልን ሲሆን ከዚህም ውስጥ እንደ አዲስ አበባ 6 ሚሊዮን አቅደን 9.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል::
የከተማችን ነዋሪ የመሪችንን ጥሪ ተቀብሎ ማልዶ በመነሳት በአስደናቂ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ችግኞችን በመትከል ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ገድል በመፈጸሙ ታላቅ አክብሮት ከምስጋና ጋር የሚገባው ሲሆን በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ያስተባበራችሁ እና የደከማችሁ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞቻችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ይህ ዛሬ ያሳየነውን የተባበረ ክንድ የሚያመጣውን ለውጥ በሌሎች የልማት ስራዎቻችን ላይ በመድገም የሃገራችንን ብልፅግና እውን እንድናደርግ ጥሪዬን አቀርባለሁ::
የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
52Dawit Dave፤ Mesi Tilahun እና 50 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.