ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ወጣቶች በአከባቢ ጥበቃ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ወጣቶች በአከባቢ ጥበቃ እና ሰላም ግንባታ ላይ የሚያደርጉት ውይይት መካሄድ ጀመረ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ወጣቶች በአከባቢ ጥበቃ እና ሰላም ግንባታ ላይ የሚያደርጉት ውይይት መካሄድ ጀመረ

ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማኅበር ጋር በመተባበር ከ12 ክልሎችና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር መከፋፈሎችን የሚያስታርቅ ወጣት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና ለአረንጓዴ ምድር" በሚል መሪ ቃል በአከባቢ ጥበቃ እና ሰላም ግንባታ ላይ ያተኮረ የወጣቶች ፎረም ውይይት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም መካሄድ ጀመረ

አቶ ቀጄላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወጣት የሚላቸው እድሜያቸው ከ 15- 24 ክልል ውስጥ የሚገኙትን መሆኑን አስታውሰው ወጣቶች በአገሪቱ ፖለቲካዊ እና የፖሊሲ አቅጣጫ ላይ እንዲሳተፈ መንግስት ምቹ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን ገልጸዋል

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ በበኩላቸው ወጣቶች ለሰላም ግንባታ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልጸው የወጣቶችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ ተቋማትን እንደሚደግፍ ገልጸዋል

ማኅበሩ የሰላም አየር የሰፈነባት አገር ለመገንባት እና በውይይት የሚያምኑ ወጣቶችን ለማፍራት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ያደነቁት አቶ ጥበቡ የአገራችን ሰላም እና አንድነት ለማስቀጠል ትልቅ ራዕይ ያላቸው ወጣቶች ህልማቸውን እውን እንዲያደርጉ ቢሮው እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል

የኢትዮጵያ ወጣቶች ውይይት ለሰላም ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጫላ አሰፋ ባስተላፉት መልዕክት ከተመሰረተ ሦስታ ዓመት ያስቆጠረው ድርጅቱ በዓለም አቀፋዊ እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት መስራቱን አስታውሰው በመወያየት የሚያምን የሰላም አየር የሰፈነባት እና ወጣት የማይጠፋባት ዓለም ለመገንባት በጋራ እንሰራለን ብለዋል

በአገራችን ባለው ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በመነጋገር ከሁሉም የተሻለች ሁሌም የምንኮራባት አገር ለመገንባት መስራት ያስፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሩ የፎረሙ አባላት ለሰላም ግንባታ እና ለአየር ንብረት ደህንነት በየክልላቸው ሲሄዱ አምባስደር ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል

ከ12 ክልሎችና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር የሚደረገው

የአዲስ ፎረም እስከ ነሐሴ 20 2016 ድረስ እንደሚቀጥል ተመልክቷል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+12

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

155Yewubdar Getnet፤ Senait Niway እና 153 ሌሎች

9

19

ይውደዱ

አስተያየት

ላክ

ያጋሩ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.