የሪፎርም ቀን ምክንያት በማድረግ ሦስቱም ተቋማት...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የሪፎርም ቀን ምክንያት በማድረግ ሦስቱም ተቋማት ለአግልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገለጸ ጳጉሜ 02 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የሪፎርም ቀን ምክንያት በማድረግ ሦስቱም ተቋማት ለአግልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገለጸ

ጳጉሜ 02 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስራ እና ከህሎት ቢሮ እና ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃበት ልማት ቢሮ ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የሪፎርም ቀን ምክንያት በማድረግ በሦስቱም ተቀቋማት እስክ 11፡30 አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገለጸ

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ባሰሙት ንግግር አዲሱ ዓመት መቃረቡን ተከትሎ የጳጉሜ አምስቱን ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች እየተከበረ እንደሚገኝ አስታውሰው ለመንግስት ሰራተኛው የተለየ ቀን የሆነውን የሪፎርም ቀን ስናከብር የምናገለግለውን ሕዝብ በአዲስ መንፈስ በተሻለ ታማኝነት እና ቃል በመግባት ልናከብረው ይገባል ብለዋል፡፡

የሁሉም የተቋሙ ሰራተኛ በሌላ በኩል ተገልጋይ መሆኑን በመረዳት አገልግሎት አሰጣጥን በጥራት በማጀብ ለአገራዊ ተልኮ በጋራ መስራት ይገባናል ያሉት አቶ ጥራቱ ግቢውን ለአገልግሎት አሰጣጣችን ምቹ ለማድረግ የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀንብሩ በበኩላቸው ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል በመላው አገሪቱ እና በአዲስ አበባ እየተከበረ እንደሚገኝ ገልጸው የላቀ ለውጥ ለማምጣት በአብሮነት እና በወንድማማችት ስራዎችን ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡

ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ሁሉም የመዲናዋ መንግስት ተቋማት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ተገኝተው ለህዝቡ የተለመደውን አገልግሎት እንደሚሰጡ የገለጹት ዶክተር ጀማሉ እንደ አገር ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተጀመሩ ሰፋፊ ስራዎችን በማስቀጠል እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት በጋራ እንስራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መዲናችን አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ለውጦች የተመዘገቡባት እና በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ ትገኛለች ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በለውጥ ላይ ያለችውን የከተማችን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የሪፎርም ስራ ተግባራዊ በማድረግ በሁሉም መዋቅሮች የተዘረጋው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ቢሮው ማሕበራዊ መስተጋብርን ለማጠንከር በርካታ መልካም አጋጣሚ ያሉትን ስፓርትን በመጠቀም የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማጠናከር እና የስፓርት ልማት ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ በአዲሱ በጀት ዓመት በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት አቶ በላይ የወጣቱን፣የስፓርት ቤተሰቡን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎችን አጠናክረን እቀጥላለን ብለዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.co HBm/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

HVAChttps://www.instagram.co ምግብm/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+8

All reactions:

99Meshu Man, አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . and 97 others


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.