
ቢሮው ከ16 ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ተፈራረመ ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ቢሮው ከ16 ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ተፈራረመ
ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በ 2017 በጀት ዓመት በሴክተር ተቋማት ቅንጅት ትብብር ትግበራ አሰራርን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ፊርማ ከ16 ተቋማት ጋር ተፈራረመ
የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት በሴክተር ተቋማት የሚሰሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የወጣቱን ጉዳይ አብይ አጀንዳ በማድረግ እንዲሰሩ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት መሆኑን ገልጸው በሀገር አቀፍ ብሎም በከተማ ደረጃ ባለፉት የለውጥ አመታት በወጣት እና በስፖርት ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦች በማጽናት በቀጣይ በማህበራዊ፣በአኪኖሚያዊ እና በፓለቲካው ዘርፍ በቅንጅት እንስራ ስር ጥሪ አቅርበዋል
ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር እና ተግባራዊ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ያደረጉትየለውጥ መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልሐሚድ ድሌቦ ሴክተሮች ድርጅቶችን በአንድ ላይ በማምጣት ችግርን በጋራ ለመፍታት ቅንጅታዊ አተገባበር ወሳኝ እንደሆነ ገልጸው ማቀድ ኃላፊነት መውሰድ መምራትና መተግበር ለውጤታማ ተቋም ወሳኝ መሆኑን አውስተዋል
አሰራሩን ከማዕከል እስከ ወረዳ ማስፋት፣ የውል ስምምነት ማድረግ ውጤቱን እየገመገሙ መለካት በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ቅንጅታዊ አስራር በመተግበር የተመዘገቡ ውጤቶችን መለካት አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተገልጽዋል
ቅንጅታዊ አሰራር የአገልግሎት ልሕቀት በመፍጠር ስራን በማሻሻል የፈጠራ ስራዎችን ለማፍለቅ አስቻይ እንደሆነ ይታመናል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.