ለአገር ባለውለታ ለሆኑ አንጋፋ የስፓርት ሰዎች...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ለአገር ባለውለታ ለሆኑ አንጋፋ የስፓርት ሰዎች እውቅና እና የክብር ካባ የማልበስ መርሃ ግብር ተካሄደ ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

ለአገር ባለውለታ ለሆኑ አንጋፋ የስፓርት ሰዎች እውቅና እና የክብር ካባ የማልበስ መርሃ ግብር ተካሄደ

ጳጉሜ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ከኢትዮጵያ አረንጓዴው ጎርፍ አትሌቲክስ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር በአትሌቲክስ እና በአሰልጣኝነት ለአገር ባለውለታ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን የካባ ማልበስ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበረከተ

ዛሬ በአራት ኪሎ ስፓርት ትምህርት ስልጠና ማዕከል በተካሄደው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የቢሮ የስፓርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉን ጨምሮ አንጋፋ አትሌቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል

በጎ አድራጎት ድርጅቱ በዛሬው መርሃ ግብሩ ለሀገራዊ የአትሌቲክስ ከፍታ እና ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ለፈጸሙት ተጋድሎ እንዲሁም በአሰልጣኝነት ዘመናቸው ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክብር ካባና ያለበሳቸው

🥇አሰልጣኝ ሻምበል ተክሌ ፈንቴሳ

🥇አሰልጣኝ ሉቺያ ይስሀቅ

🥇አትሌት 50አለቃ ሃይሉ ወ/ፃዲቅ

🥇አቶ ኤርምያስ አየለ መሆናቸው ታውቋል

በዕውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ባስተላለፉት መልዕክት ስፖርቱ በዓለም አደባባይ ያስጠሩ የኢትዮጵያ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ያስመሰከሩ ወገኖቻችንን በሉአላዊነት ቀን ማክበራችን ዝግጅቱን ለየት ያደርገዋል ብለው ትላንት ለአገር የከፋሉትት ዋጋ በማስታወስ የዛሬ አንጋፎችን ማመስገን የሚበረታታ እና ጀግኖችን ማክበር በሁሉም መስክ ሊለመድ ይገባል ብለዋል

ስመ ጥርና አንጋፋ አትሌቶቻችን ለአገር የከፈሉት ዋጋ የማይረሳ እና በክብር ሁሌም በታሪክ የሚወሳ ነው ያሉት የኢትዮጵያ አረንጓዴ ጎርፍ አትሌትክስ በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና የአዲስ አበባ አትሌትክስ ፌደረሽን ፕሬዘዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ በቦርዱ በሙሉ ድምፅ ታምኖባቸው የተሸለሙት አሰልጣኞች የሰሩት ስራ አሻራ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ታትሞ የሚኖር ነው ብለዋል

የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.