
ፋሲል ከተማ የ18ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ሻምፒዮና ሆነ መስከረም 05 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ፋሲል ከተማ የ18ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ሻምፒዮና ሆነ
መስከረም 05 ቀን 2016ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
18ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ታድየም ፍፃሜውን ሲያገኝ ፋሲል ከተማ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክን 2 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮና ሆኗል።
ለፋሲል ከተማን የማሸነፊያ ጎሎች ማርቲን ኩዞ እና አፍቅሮት ሰለሞን ሲያስቆጥሩ የፋሲል ከተማው ኤፍሬም ሀይሉ የእለቱ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
ከነሐሴ 28 /2016ዓ.ም ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ሲካሄድ በቆየው እና ዛሬ ፍፃሜውን ባገኝው 18ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አምስት ክለቦች የተሳተፋበት ሲሆን ፋሲል ከተማ የውድድሩ ሻምፒዮና በመሆን የወርቅ ሜዳልያ እና የዋንጫ ሽልማት ሲበረከትለት ኢትዮ ኤሌክትሪክ የብር ሜዳልያ ባለቤት መሆን ችሏል
መቻል የስፖርት ክለብን በደረጃ ጨዋታ ያሸነፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶሰተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ መሆን ችሏል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.