
የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን በሰላም እና በአብሮነት ለማክበር ከአጎራባች ከተሞች ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው። አቶ አቶ ጥበቡ በቀለ መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን በሰላም እና በአብሮነት ለማክበር ከአጎራባች ከተሞች ከሚገኙ ወጣቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው። አቶ አቶ ጥበቡ በቀለ
መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የመስቀል እና የኢሬቻ በአላት በሰላም፣ በአንድነት እና በፍቅር እንዲከበር የሚያስችል ውይይት በከተማዋ በሁሉም አከባቢዎች ከሚገኙ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ጋር እያካሄደ ይገኛል።
ዛሬ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከክፍለ ከተማው እና ከአጎራባቹ ከቡራዩ ከተማ ከመጡ ወጣቶች ጋር የመስቀል እና የኢሬቻ በአላት አከባበር ዙሪያ ውይይት ተደርጎሎል።
በውይይቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ የኢሬቻ እና የመስቀል በዓላት የአደባባይ በአላት እንደመሆናቸውና በአላቱን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ በርካታ እንግዶች ስላሉ በአላቱ በሰላም ለማክበር ከአጎራባች ከተማች ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ወጣቱ የአብሮነት የአንድነት የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት መገለጫ የሆኑትን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላትን ሲያከብር ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቆ በማክበር ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ አደራ አለበት ብለዋል አቶ ጥበቡ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ በበኩላቸው የመስቀል እና የደመራ በዓላት በተባበሩ መንግስታት ትምህርት እና ሳይንስ UNSCO በማይዳሰሱ ቅርስነት የተመዘገቡ በመሆኑ በዓላትን ስናከብር የሀገራችን መልካም ገፅታ በሚገነባ መልኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በዓላቱን በሰላም እንዲከበሩ በከተማው ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት እየተደረገ እና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ወ/ሮ ቆንጅት ተናግረዋል
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና የቡራዩ ከተማ ወጣቶችም በዓላቱን በሰላም እንዲከበሩ በቅንጅት በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.