
የመስቀል መደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ለሚያስተባብሩ ከ310ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ ስምሪት ተሰጠ። መስከረም 13 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የመስቀል መደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ለሚያስተባብሩ ከ310ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ ስምሪት ተሰጠ።
መስከረም 13 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም ፀጥታ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በመሆን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓልን በሰላም እንዲከበር ለሚያስተባብሩ ከ310ሺህ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ ስምሪት ሰጥተዋል።
በዓላቱ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ቱፊታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበር የከተማው ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በተሰጣቸው ስምሪት መሰረት እንዲሰሩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ተስፋዬ ደንድር አሳስበዋል።
በአላቱ የሚከበሩባቸው ባታዎች እንዲሁም የአከባቢያቸውን ብሎም የከተማቸውን ሰላም ወጣቶች ነቅተው እንዲጠብቁ የተናገሩት አቶ ተስፋዬ በበዓላቱ እንዳይያዙ የተከለከሉ ነገሮችን እና በኮሪደር ልማት የተሰሩ የልማት ስራዎችን እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል።
ከከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ጋር ከክፍለ ከተማ እስከ ብሎክ በመስቀል እና በኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት ተከታታይነት ያለው መደረጉን እና የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ያስታወሱት አቶ ዳዊት ትርፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ዛሬ በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ ውይይት እና የስራ ስምሪት እንደተሰጠ ተናግረዋል።
ወጣቱ ትውልድ ከአባቶቹ የተቀበላቸው ባህሎች እና ታሪኮች በሚገባ ተረድቶ እና እሴቶቻችን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ ታሪካዊ አደራ እንዳለበትም አቶ ዳዊት አሳስበዋል።
በከተማ ደረጃ በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ ጥምር የሰላም እና የፀጥታ ግብረ ሀይል መቆቆሙን እና ወደ ስራ መግባቱን የተናገሩት ረዳት ኮማንደር አይናለም በየነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የማህበረሰብ ፖሊስ አገልግሎት ሀላፊ ወጣቶች ከተቆቆመው ግብረ ሀይል ጋር በመቀናጀት እንዲሰሩ ተናግረዋል
በማጠቃለያ ውይይቱ እና በስራ ስምሪቱ ላይ የተገኙ የከተማው ወጣቶች የመሰቀል እና የኢሬቻ በአላት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በተሰጣቸው የስራ ስምሪት መሰረት ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በዓላቱን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ የግዳ አቀባበል ስነ ምግባር እንግዶችን ተቀብለው በማሰተናገድ እንደሚሸኙ ወጣቶቹ የተናገሩ ሲሆን በዓላቱ ካለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩ እጅ ለእጅ ተያይዘው እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል ።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.