አበበ ቢቂላ ስቴዲየም ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

አበበ ቢቂላ ስቴዲየም ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱበት ለማድረግ እየተሰራ ነው። አቶ ዳዊት ትርፋ መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

አበበ ቢቂላ ስቴዲየም ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱበት ለማድረግ እየተሰራ ነው። አቶ ዳዊት ትርፋ

መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ከፍተኛ ከመራሮች በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በመመልከት በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀመጠ።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ ሲያስረዱ በአበበ ቢቂላ ስቴድየም ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ ታስቦ እየተሰራ ያለውን ስራ በመመልከት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ገልጸው የተጀመረው ስራ በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ጥሪ አቅርበዋል

ቢሮው የስፓርት ቤተሰቡን እና የወጣቶች ጥያቄ ለመመለስ በአዲሱ በጀት ዓመት በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ዳዊት ከተማችን የሚመጥኑ የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና ስቴድየሞች ግንባታ መፋጠን ሁሉን አቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን እውን ለማድረግ ያስችላል ብለዋል

ቢሮው የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ሁኔታ በቅርበት በመከታተል ተገቢውን እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጹት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቢሮ የስፓርትና ትምህርትና ስልጠ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሚሽነር ተስፋዬ ኦሜጋ በአበበ ቢቂላ ስቴድየም ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ እየተከናወነ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.