የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን አስመልክቶ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን አስመልክቶ ከሸገር ከተማ ወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ። መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን አስመልክቶ ከሸገር ከተማ ወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት ተካሄደ።

መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ/ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት እና ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በጋራ በመሆን የዓለም አቀፍ የሠላም ቀንን ምክንያት በማድረግ የለሚ ኩራ ወጣቶች ከአጎራባቻ የሸገር ከተማ ወጣቶች ጋር በመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሄደ

በፓናል ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች የሸገር ከተማ የወጣቶች ሊግ አመራሮች፣የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ ኃልፊዎች የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ወጣቶች ተሳትፈዋል

ኢትዮጵያውያን በወርሀ መስከረም በጋራ ከምናከብረው የዘመን መለወጫ በዓል በተጨማሪ ህብረብሔራዊነትን የሚያሣዩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላት አብሮነታችን የሚያሳዩ በዓላት ናቸው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ በርካታ ህዝብን ተሳታፊ የሚያደርጉት በዓላት እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በአብሮነት፣በወንድማማችነትና እህታማማችነት መንፈስ በማክበር ጠንካራ ህብረታችንን ማሳየት ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪ ወጣት አንሙት አበጀ በበኩላቸው አዲስ አበባ ለሸገር ከተማ ሸገር ከተማ ለአዲስ አበባ በሚል እሳቤ ከአጎራባች የሸገር ከተሞች ጋር ውይይት መደረጉ በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ሠላም መተኪያ የሌለው ለአንድ አገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማዝገንዘብ በዓላቱ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ጠንክር የክፍለ ከተማው ወጣቶች እና የሸገር ከተማ ወጣቶች በሰላም እና በልማት ጉዳይ በጋራ የሚሰሩት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓል

ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሁለቱ ከተማ ወጣቶች በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረግልግጠዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.