ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ደ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ደማቅ ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ደማቅ ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

መስከረም 19 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ኢሬቻ ማስ ስፖርት በሚል በመሪ ሀሳብ ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ በልደታ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት ከሜክሲኮ ወደ ሳር ቤት በተሰራው የኮሪደር ልማት ላይ አካሄደ።

በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በእግር ጉዞው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ኢሬቻ ማስ ስፓርት ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ኢሬቻን በባለቤትነት የሚያከብሩበት መሆኑን ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ ከመሆኑ ባሻገር በዓሉ ስፓርት ለጤንነት ከሚሰጠው ዋጋ ባልተናነስ ስለ ጤና አብዝቶ የሚጸለይበት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኢሬቻ ወጣት፣ አዛውንት፣ ህፃን፣ አዋቂ ሳይል፣ በሀይማኖት ሳይለያይ፣ በፖለቲካ ሳይነጣጠል ሁሉም ማህበረሰብ በአንድነት የሚያከብረው የአብሮነት መገለጫ ነው ያሉት አቶ በላይ ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነውን ኢሬችን ስናከብር ለእድገታችን፣ለሰላማችን እና ለአንድነታችን በጋራ መቆማችንን ለማሳየት ነው ብለዋል።

የህብረተሰቡን በተላይ የወጣቱን የዘወትር ጥያቄ የሆነውን የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ በከተማ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ያሳወቁት አቶ በላይ በከተማችን እየተሰሩ ባሉ የኮሪደር ልማቶች ላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተካተው መሰራታቸው የዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ሀላፊ አቶ ማቲዮስ ሰቦቃ በበኩላቸው ኢሬቻ የአብሮነት የአንድነት የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት መገለጫ በዓል መሆኑን ተናግረው በአዲስ አበባ በዓሉን በአማረ በደመቀ እና በሰለም ለማክብረ እየተሰሩ ላሉ ሁለንተናዊ ስራዎች ምስጋና አቅርበዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በስተላለፋት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የብዙሐን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ ባሻገር የኢሬቻ በዓልን ይበልጥ ለአለም ለማስተዋወቅ የሚረዳ ነው ብለዋል።

የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተካሄደው የብዙሐን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የእግር ጉዞ ፕሮግራም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ እና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች የስፖርት ቤተሰቦች እና ከአዲስ አበባ አጎራባች ከተማች የመጡ ወጣቶች ተሳትፈውበታል።

የ2017 የኢሬቻ በዓል ”ኢሬቻ ለባህላችን ሕዳሴ” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 25 በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንደሚከበር በዝግጅቱ ተገልጽዋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.